Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ሰው ለጌታ የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ለእግዚአብሔር ስለሚቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ነው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 7:11
12 Cross References  

ውኃም ካለበት ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለት መቶ አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፤ ይህ እንዲያስተሰርይላችሁ እህል ቁርባን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለሰላም መሥዋዕት ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቁርባን በጠቅላላ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ እያንዳንዱም እንደሌላው ወንድሙ ይደርሰዋል።


ለአንድነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሶገር ልጅ የናትናኤ መባ ይህ ነበረ።


የጌታንም መሠዊያ ደግሞ አደሰ፥ የአንድነትንና የምስጋናንም መሥዋዕት ሠዋበት፤ ይሁዳም የእስራኤልን አምላክ ጌታን እንዲያገለግሉ አዘዘ።


“መሥዋዕትንና የደኅንነት ቁርባንን ማቅረብ ነበረብኝ፥ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ።


የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለአንድነት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለጌታ የአንድነትን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቁርባኑን ለጌታ ከሰላሙ መሥዋዕት ያመጣል።


መሥዋዕታችሁን በሠዋችሁበት ዕለትና በማግስቱ ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ማናቸውም ነገር ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል።


የምስጋናንም መሥዋዕት ለጌታ ስትሠዉ እንዲሠምርላችሁ አድርጋችሁ ሠዉት።


ሕዝቅያስም፦ “አሁን ለጌታ ተቀድሳችኋል፤ ቅረቡ፥ መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ ጌታ ቤት አምጡ” ብሎ ተናገረ። ጉባኤውም መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት አመጡ፤ ልባቸውም የፈቀደ ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አመጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements