Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 5:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ማንኛውም ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዞች ሳያውቅ አንዱን ተላልፎ ቢገኝ በደለኛ ነው፤ በኀጢአቱም ይጠየቅበታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “አንድ ሰው ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዲቱን ቢተላለፍ በደለኛ ይሆናል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 5:17
11 Cross References  

“ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ባለማወቅ ጌታ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ተላልፎ ኃጢአት ቢሠራና ቢበድል፥


“የእስራኤል ማኅበር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገሩም ከጉባኤው ፊት ቢሸሸግ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ሠርተው ቢበድሉ፥


አገልጋይህ ደግሞ ይጠብቀዋል፥ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።


“ማናቸውም ሰው ቢተላለፍ፥ ሳያውቅም ለጌታ በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኃጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለጌታ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያመጣል፤ ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ በብር ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ለበደል መሥዋዕት ያቀርበዋል።


“አንድ ገዢም ኃጢአትን ቢሠራ፥ ጌታም አምላኩ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ አንዱን ባለማወቅ ሠርቶ ቢበድል፥


ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።


የሚጠራጠር ሰው ቢበላ ግን በእምነት ስላልሆነ ተኰንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው።


ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው እንደ ግምጋሜህ መጠን ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሠራው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።


እርሱም የበደል መሥዋዕት ነው፤ በእውነት በጌታ ፊት በደለኛ ነው።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements