ዘሌዋውያን 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 “ማንም ሰው የመሓላን ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ ወይም ስለ ነገሩ አይቶ ወይም አውቆ ባይናገር፥ ኃጢአት መሥራቱ ነውና በደሉን ይሸከማል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 “ ‘አንድ ሰው ስላየውና ስለሚያውቀው ነገር ሕጋዊ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ተጠይቆ ቃሉን ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆን፣ ይህ ሰው ኀጢአት ሠርቷልና ይጠየቅበታል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 “አንድ ሰው በፍርድ አደባባይ በይፋ ለምስክርነት መጥቶ ያየውን ወይም ስለ ጉዳዩ የሚያውቀውን ነገር ባይመሰክር ኃጢአት ይሆንበታል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 “አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ማንም ሰው የሚያምለውን ቃል ቢሰማ፥ ምስክር ሆኖም አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ ወይም አውቆ እንደ ሆነ ባይናገር፥ ኃጢአት መሥራቱ ነውና በደሉን ይሸከማል። See the chapter |