Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 27:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከበሬም ሁሉ ከዐሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከዐሥር አንድ ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከቀንድ ከብቶች፣ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ የሚወጣው ዐሥራት ከእረኛ በትር በታች ከሚያልፉት ዐሥረኛው እንስሳ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከቤት እንስሶች ከዐሥር አንዱ እጅ የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ እንስሶች በሚቈጠሩበት ጊዜ ከዐሥር አንዱ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከበ​ሬም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከበ​ግም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከእ​ረ​ኛ​ውም በትር በታች ከሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 27:32
6 Cross References  

በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ መንጋውን በሚቆጥረው ሰው እጅ ሥር እንደገና ያልፋሉ፥ ይላል ጌታ።


ከበትርም በታች አሳልፋችኋለሁ ወደ ቃል ኪዳንም እስራት አገባችኋለሁ፤


በአትክልት ቦታ መካከል ባለው ጥሻ ብቻቸውን የተቀመጡት የርስትህን መንጋ፥ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀደመው ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


ሰውም አሥራቱን ሊቤዥ ቢወድድ፥ በእርሱ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበት።


ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፥ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”


ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ሁሉ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements