ዘሌዋውያን 25:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 “ማናቸውም ሰው ቅጥር ባለው ከተማ ውስጥ ያለ መኖሪያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት የመቤዠት መብት አለውና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 “ ‘ማንኛውም ሰው ቅጥር በተሠራለት ከተማ ውስጥ የሚገኝ መኖሪያ ቤቱን ቢሸጥ ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ሊዋጀው ይችላል፤ የመዋጀት መብቱ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 “አንድ ሰው ቅጽር በተሠራላት ከተማ ውስጥ ቤት ቢሸጥ ከተሸጠበት ዕለት ጀምሮ በአንድ ዓመት ውስጥ መልሶ የመዋጀት መብት አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 “ሰውም ቅጥር ባለበት ከተማ መኖርያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት መቤዠት ይችላል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ሰውም ቅጥር ባለበት ከተማ መኖሪያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት መቤዠት ይችላል። See the chapter |