ዘሌዋውያን 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 በስብራት ፋንታ ስብራት፥ በዐይን ፋንታ ዐይን፥ በጥርስ ፋንታ ጥርስ ይሁን፤ በሰው ላይ ጉዳት ያደረገ ሰው እንዲሁ ይደረግበት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ይኸውም ስብራት በስብራት፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ ማለት ነው። በሌላው ሰው ላይ ያደረሰው ጕዳት በርሱም ላይ ይድረስበት፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 የሌላውን ሰው አጥንት ቢሰብር አጥንቱ ይሰበር፤ የሌላውን ሰው ዐይን ቢያወጣ ዐይኑ ይውጣ፤ ጥርስም ቢሰብር ጥርሱ ይሰበር። በሌላ ሰው ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ቢያደርስ የዚያው ዐይነት ጒዳት በእርሱ ላይ ይመለስበት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ስብራት በስብራት ፋንታ፥ ዐይን በዐይን ፋንታ፥ ጥርስ በጥርስ ፋንታ፥ ሰውን እንደ ጎዳ እንዲሁ ይደረግበት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ስብራት በስብራት ፋንታ፥ ዓይን በዓይን ፋንታ፥ ጥርስ በጥርስ ፋንታ፥ ሰውን እንደ ጐዳ እንዲሁ ይደረግበት። See the chapter |