Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 23:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን ለጌታ የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በዚያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ለሰባት ቀንም ቂጣ ብሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዐሥራ አምስተኛው ቀን የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ከዚያን በኋላ እስከ ሰባት ቀን ድረስ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትመገባላችሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን ለእግዚአብሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ብሉ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 23:6
9 Cross References  

ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለጌታ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።


“የቂጣውን በዓል ጠብቀው፤ በአቢብ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።


ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ በዓል አድርጋችሁ ጠብቁት፥ ለጌታ በዓል ነው፤ ለትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ።


የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።


የቦካውን ቂጣ ከእርሱ ጋር አትብላ፥ ከግብጽ አገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብጽ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ ይህን ቂጣ፥ እርሱም የመከራን እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements