Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 23:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ሰባት ቀን ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ፤ በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ፤ ዋና ጉባኤ ነው፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሰባት ቀን መሥዋዕቱን በእሳት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ መሥዋዕትን በእሳት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የተለመደ ተግባራችሁንም አታከናውኑበት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ከሰባቱም ቀኖች በእያንዳንዱ ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠል የምግብ መሥዋዕት አቅርቡ፤ ይህም ጉባኤውን የምትፈጽሙበት ቀን ስለ ሆነ ምንም ሥራ አትሥሩበት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ሰባት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ ስም​ን​ተ​ኛ​ዋም ቀን የተ​ቀ​ደ​ሰች ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ የመ​ሰ​ና​በቻ በዓል ነውና፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባንን አቅርቡ፤ በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፥ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠለውን ቍርባን አቅርቡ፤ ዋና ጉባኤ ነው፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 23:36
8 Cross References  

ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕዝራ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛው ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።


ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።


በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥


ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ ጌታ ቤት ሰብስቡ፥ ወደ ጌታም ጩኹ።


ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለጌታ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።


በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements