Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ካህኑ ግን ባርያ በገንዘቡ ቢገዛ እርሱ ይብላ፤ በቤቱም የተወለዱት ለእርሱ ከሆነው እንጀራ ይብሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ነገር ግን ካህኑ በገንዘብ የገዛው ወይም በቤቱ የተወለደ ባሪያ ቢኖረው፣ ያ ባሪያ ከካህኑ ድርሻ መብላት ይችላል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ካህኑ በገንዘቡ የገዛው ወይም በቤቱ የተወለደ አገልጋዩ ግን የካህኑ ድርሻ ከሆነው ምግብ ይብላ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ካህኑ ግን በገ​ን​ዘቡ አገ​ል​ጋይ ቢገዛ እርሱ ከም​ግቡ ይብላ፤ በቤ​ቱም የተ​ወ​ለ​ዱት ከእ​ን​ጀ​ራው ይብሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ካህኑ ግን በገንዘቡ ባሪያ ቢገዛ እርሱ ይብላው፤ በቤቱም የተወለዱት ከእንጀራው ይብሉ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 22:11
7 Cross References  

በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆናል።


በብር የተገዛ የማንም ባርያ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ከእርሱ ይብላ።


አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።


የካህንም ልጅ ምእመንን ብታገባ፥ እርሷ ከተቀደሰው ቁርባን አትብላ።


እጅግ ቅዱስ የሆነውን እና የተቀደሰውን የአምላኩን እንጀራ ይብላ፤


በእሳት ከሚቀርበው እጅግ ከተቀደሰው ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ የእህሉ ቁርባናቸው ሁሉ፥ የኃጢአታቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ለአንተ ለልጆችህም እጅግ የተቀደሰ ይሆናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements