ዘሌዋውያን 20:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ስለዚህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ርኩስ ከሆነው ትለያላችሁ፤ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ላይ በሚርመሰመሱ ነፍሳት ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 “ ‘ንጹሕ በሆኑትና ንጹሕ ባልሆኑት እንስሳት እንዲሁም ንጹሕ በሆኑትና ንጹሕ ባልሆኑት ወፎች መካከል ልዩነት አድርጉ። ርኩስ ነው ብዬ በለየሁት በማንኛውም እንስሳ ወይም ወፍ ወይም በምድር ላይ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም ነገር ራሳችሁን አታርክሱ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ስለዚህም ንጹሓን በሆኑትና ንጹሓን ባልሆኑት እንስሶችና ወፎች መካከል ልዩነት አድርጉ፤ እኔ ርኩሳን ናቸው ብዬ ለይቼ ባስታወቅኋችሁና በምድር ላይ በሚገኙ እንስሶች፥ ወፎችና ሌሎችም ነገሮች ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 እንግዲህ በንጹሕና በርኩስ እንስሳ መካከል፥ በንጹሕና በርኩስም ወፍ መካከል ለየሁላችሁ፤ ርኩሳን ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ፥ በምድርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ነፍሳችሁን አታርክሱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 እንግዲህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ከርኩስ ትለያላችሁ፤ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ነፍሳችሁን አታርክሱ። See the chapter |