Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ዝሙት ነው፤ በመካከላችሁ አመንዝራ እንዳይኖር እርሱና እነርሱ በእሳት ይቃጠሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ አድራጎቱ ጸያፍ ነው፤ በመካከላችሁ እንዲህ ዐይነት ርኩሰት እንዳይገኝ ሰውየውና ሴቶቹ በእሳት ይቃጠሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንድ ሰው እናትና ሴት ልጅዋን ቢያገባ፥ ስለ ፈጸሙት ክፉ ድርጊት ሦስቱም በእሳት ተቃጥለው ይገደሉ፤ እንዲህ ያለው ነገር በመካከላችሁ መፈጸም የለበትም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ማና​ቸ​ውም ሰው እና​ቲ​ቱ​ንና ልጂ​ቱን ቢያ​ገባ ኀጢ​አት ነው፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆን እር​ሱ​ንና እነ​ር​ሱን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ በእሳት ይቃጠሉ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 20:14
6 Cross References  

የሴትንና የሴት ልጇን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጇን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጇን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ እርሷን አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው።


“‘ከዐማቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


የድሆችን ራስ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ የትሑታንንም መንገድ ያጣምማሉ፤ ቅዱሱንም ስሜን ለማርከስ አባትና ልጅ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፤


እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የጌታን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል ፈጽሟልና እርሱና የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠል።’ ”


ኢያሱም፦ “ለምን መከራን አመጣህብን? ጌታ ዛሬ መከራን ያመጣብሃል” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።


የካህንም ልጅ ራስዋን በዝሙት ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ በእሳት ትቃጠል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements