Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 20:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘አንድ ወንድ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ እንደሚፈጽም ሁሉ ከወንድ ጋራ ቢፈጽም፣ ሁለቱም አስጸያፊ ድርጊት ፈጽመዋልና ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አንድ ወንድ ከሌላው ወንድ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርግ የረከሰ ሥራ ስለ ሠሩ ሁለቱም ይገደሉ፤ ለመሞታቸውም ኀላፊነቱ የራሳቸው ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ማና​ቸ​ውም ሰው ከሴት ጋር እን​ደ​ሚ​ተኛ ከወ​ንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድ​ር​ገ​ዋል፤ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 20:13
9 Cross References  

ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥


ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነው።


ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለሐሰተኞችም፥ በውሸትም ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው።


እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


“ከእስራኤል ወንድ ወይም ሴት የቤተጣዖት አመንዝራ አይሁን።


ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፦ “በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።”


በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፥ ጥቂት የከተማይቱ ወስላቶች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፥ “ዝሙት እንድንፈጽም በት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት።


ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ቤት አታቅርብ፥ ሁለቱም በጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements