ዘሌዋውያን 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 “ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 “ ‘ማንኛውም ሰው የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ዱቄቱ የላመ ይሁን፤ ዘይት ያፍስስበት፤ ዕጣንም ይጨምርበት፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ማነኛውም ሰው ለእግዚአብሔር የእህል መባ በሚያቀርብበት ጊዜ ምርጥ ዱቄት መሆን አለበት፤ በእርሱም ላይ የወይራ ዘይትና ዕጣን ይጨምርበት፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 “ማናቸውም ሰው ቍርባን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሆን ቢያቀርብ፥ ቍርባኑ ከመልካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስስበታል፤ ነጭ ዕጣንም ይጨምርበታል፤ ይህም መሥዋዕት ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለእግዚአብሔር ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስስበታል፥ በ ዕጣንም ይጨምርበታል፤ See the chapter |