ዘሌዋውያን 19:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 “ወደ ምድሪቱም ገብታችሁ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁ ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት ለእናንተ እንዳልተገረዘ ይሆናል፤ አይበላም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 “ ‘ወደ ምድሪቱ ገብታችሁ ማንኛውንም ዐይነት ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ፣ ፍሬው ለመብላት ያልተገረዘ መሆኑን ዕወቁ፤ ለሦስት ዓመትም የተከለከለ በመሆኑ አይበላ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 “ወደ ከነዓን ምድር ገብታችሁ ማንኛውንም ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ እስከ መጀመሪያው ሦስት ዓመት ድረስ የሚሰጠውን ፍሬ መብላት የተከለከለ መሆኑን አስታውሱ። በእነዚህም ዓመቶች ውስጥ ፍሬው አይበላም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 “አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ ከርኵሰቱ ሁሉ ታጠሩታላችሁ፤ የሦስቱ ዓመት ፍሬም ርኩስ ነው፤ አይበላም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ወደ አገሩም በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት እንዳልተገረዘ ይሆንላችኋል፤ አይበላም። See the chapter |