Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 19:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 መስማት የተሳነውን አትስደብ፥ በዓይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘ደንቈሮውን አትርገም፤ በዐይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ደንቆሮውን አትስደብ፤ ዐይነ ዕውሩንም ለማሰናከል በፊቱ እንቅፋት አታኑር፤ አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ደን​ቆ​ሮ​ውን አት​ስ​ደብ፤ በዕ​ው​ርም ፊት ዕን​ቅ​ፋት አታ​ድ​ርግ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ደንቆሮውን አትስደብ፥ በዕውርም ፊት ዕንቅፋት አታድርግ፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 19:14
14 Cross References  

“‘ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፥ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


“በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


እንግዲህ ከዚህ በኋላ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ከመፍረድ ይልቅ ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይወስን።


እኔም ጌታ አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያታልል፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።


ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበለዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር አሉና።


ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደውባቸው ነበር፥ ምግብ፥ ወይና አርባ ሰቅል ብር ከእነሱ ይወስዱ ነበር፤ አገልጋዮቻቸው ደግሞ ሕዝቡን ይጨቁኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፥ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።


የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ።


በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ።


ለአይሁድም ይሁን ለግሪክም እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ማሰናከያ አትሁኑ።


“ፍርድን ፈጽሞ አታጓድሉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ።


የጥበብ መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ የሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋልን ያገኛሉ፥ ውዳሴውም ለዘለዓለም ይኖራል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements