Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 16:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደተቀደሰው ስፍራ የገባውን፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቆዳቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ደማቸው ለማስተስረያነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባው፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡት ወይፈንና ፍየል ከሰፈር ውጭ ተወስደው ቈዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸው ይቃጠል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆነው የቀረቡትና ኃጢአትን ለማስተስረይ ደማቸው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የነበረው ኰርማና ፍየልም ከሰፈር ወደ ውጪ ተወስደው በእሳት ይቃጠሉ፤ እንዲሁም ቆዳቸው፥ ሥጋቸውና የሆድ ዕቃቸው በሙሉ ይቃጠል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደ መቅደስ የገባውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ወደ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቁርበታቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 16:27
8 Cross References  

ነገር ግን በመቅደሱ ውስጥ ለማስተስረያ እንዲሆን ከደሙ ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባው የኃጢአት መሥዋዕት ሁሉ አይበላም፤ በእሳት ይቃጠላል።”


ወይፈኑንም ከሰፈሩ ውጭ ይወስዳል፥ የፊተኛውንም ወይፈን እንዳቃጠለ ያቃጥለዋል፤ ይህ የማኅበሩ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ወይፈኑን፥ ቆዳውንም፥ ሥጋውንም፥ ፈርሱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለ።


ልብሱንም ያወልቃል፥ ሌላም ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ተሸክሞ ከሰፈሩ ውጭ ወደ ሆነ ወደ ንጹሕ ስፍራ ያወጣዋል።


ካህኑም የሚያቀርበው የእህል ቁርባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃጠላል፤ ከእርሱም አንዳች አይበላም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements