ዘሌዋውያን 15:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 እንዲሁም በወር አበባዋም ለታመመች፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ የረከሰችንም ሴት ለሚገናኝ ሰው ሕጉ ይህ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት፣ ፈሳሽ ነገር የሚወጣቸውን ወንድ ወይም ሴት፣ በሥርዐቱ መሠረት ርኩስ ከሆነች ሴት ጋራ የሚተኛውን ወንድ በሚመለከት ሕጉ ይኸው ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 እንዲሁም የወር አበባ በማየት ላይ ስላለች ሴት ወይም ወንድም ሆነ ሴት ፈሳሽ ነገር ከሰውነታቸው በሚወጣ ጊዜ ወይም ካልነጻች ሴት ጋር ስለሚተኛ ወንድ የተሰጠ መመሪያ ይህ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 በግዳጅዋም ደም ለሚፈስሳት፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ ከረከሰችም ሴት ጋር ለሚተኛ ሰው ሕጉ ይህ ነው።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 በመርገምዋም ለታመመች፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ የረከሰችንም ሴት ለሚገናኝ ሰው ሕጉ ይኸው ነው። See the chapter |