ዘሌዋውያን 15:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ፈሳሹም ነገር በሚፈስስበት ጊዜያት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በወር አበባዋ ጊዜ እንደነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ እንደ ወር አበባዋ ርኩስነት ርኩስ ይሆናል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ደሟ መፍሰሱን በቀጠለበት ጊዜ ሁሉ፣ የምትተኛበት ማንኛውም መኝታ ልክ በወር አበባዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ርኩስ ይሆናል፤ የምትቀመጥበትም ማንኛውም ነገር ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ ርኩስ ይሆናል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 በዚህም ጊዜ የምትተኛበትም አልጋ ሆነ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ደምዋም በሚፈስስበት ወራት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በግዳጅዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ እንደ ግዳጅዋ ርኩስነት ርኩስ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ደምዋም በሚፈስስበት ወራት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በመርገምዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ እንደ መርገምዋ ርኩስነት ርኩስ ነው። See the chapter |