ዘሌዋውያን 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ከለምጽ ደዌ በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፤ ከዚያም ንጹሕ ነህ ይለዋል፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ በተንጣለለው ሜዳ ላይ እንዲበር ይለቀዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ከተላላፊ በሽታ የሚነጻውንም ሰው ሰባት ጊዜ ይርጨው፤ መንጻቱንም ያስታውቅ፤ በሕይወት ያለውንም ወፍ ወደ ውጭ ይልቀቀው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ደሙንም ከሥጋ ደዌ በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይርጭ፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅለታል፤ በሕይወት ያለውንም ወፍ ወደ ሜዳ እንዲበር ይለቀዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ከለምጹም በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል፤ ንጹሕም ይሆናል፤ ያልታረደችውን ዶሮ ወደ ሜዳ ይለቅቃታል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ከለምጹ በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል፤ ንጹሕም ነው ይለዋል፥ ሕያውንም ወፍ ወደ ሜዳ ይለቅቀዋል። See the chapter |