ዘሌዋውያን 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ካህኑም ከበደል መሥዋዕት ደም ይወስዳል፤ እርሱም የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት ያስነካዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ካህኑ ከበደል መሥዋዕቱ ደም ወስዶ የሚነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ታችኛውን ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ካህኑም ከጠቦቱ ደም ጥቂት ወስዶ የነጻ መሆኑን በሚያስታውቅለት ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንና የቀኝ እግሩን አውራ ጣቶች ይቀባ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ካህኑም ከበደል መሥዋዕት ደም ወስዶ የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት ይቀባዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ካህኑም ከበደል መሥዋዕት ደም ወስዶ የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት ያስነካዋል። See the chapter |