ዘሌዋውያን 13:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)55 ደዌው ያለበት ነገር ከታጠበ በኋላ ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው ባይሰፋ ነገር ግን መልኩን ባይለውጥ፥ እርሱ ርኩስ ነው፤ በእሳት አቃጥለው፤ የለምጽ ደዌው ምልክቱ በውስጥ ወይም በውጭ ቢሆን እየሰፋ የሚሄድ ደዌ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም55 ደዌው ያለበት ዕቃ ከታጠበ በኋላ ካህኑ ይመርምረው፤ ደዌው ባይስፋፋም እንኳ መልኩን ካልለወጠ፣ ርኩስ ነው፤ ደዌው የወጣው በውስጥም ሆነ በውጭ ዕቃው በእሳት ይቃጠል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም55 ከዚህም በኋላ እንደገና ይመርምረው፤ ምንም እንኳ በማፋግ ባይስፋፋ የሻጋታው ቀለም ካልተለወጠ በቀር፥ አሁንም ርኩስ ነው፤ ከፊትም ሆነ ከኋላ ሻጋታ ወይም የመበስበስ መልክ የሚታይበት ያ ልብስ ይቃጠል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)55 ደዌውም ከታጠበ በኋላ ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው መልኩን ባይለውጥ፥ ባይሰፋም፥ ርኩስ ነው፤ በእሳት ያቃጥሉታል፤ በልብሱም ውስጥ በማጉም፥ በድሩም ወጥቶአልና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)55 ደዌውም ከታጠበ በኋላ ካህኑ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው መልኩን ባይለውጥ ባይሰፋም፥ ርኩስ ነው፤ በእሳት አቃጥለው፤ ምልክቱ በውስጥ ወይም በውጭ ቢሆን እየፋገ የሚሄድ ደዌ ነው። See the chapter |