Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እርያም ሰኮናው ለሁለት ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ዐሣማ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ዐሳማዎችንም አትብሉ፤ እነርሱ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩ በእናንተ ዘንድ እንደ ርኩስ የሚቈጠሩ ይሁኑ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እር​ያም ሰኰ​ናው ተሰ​ን​ጥ​ቆ​አል፤ ነገር ግን ስለ​ማ​ያ​መ​ሰኳ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እርያም ሰኮናው ተሰንጥቍል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 11:7
11 Cross References  

በመሀከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ መናፈሻ ስፍራው ለመግባት ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፥ የእሪያንም ሥጋ፥ አስጸያፊ ነገርንም፥ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ።


በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤


በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፥ ምሽቱንም በስውርም ስፍራ የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። ማሰሮዎቻቸው በረከሰ ነገር የተሞሉ ናቸው።


ዐሣማም፥ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩህ፥ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥምባቸውንም አትንኩ።


ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች አንዱ ጋር ተጠጋ፤ እርሱም ዐሣማ እንዲያሰማራ ወደ ሜዳ ላከው።


አጋንንቱም ከሰውዬው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ሐይቁ ተጣድፎ በመውረድ ሰጠመ።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


ለሁለት የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ።


ጥንቸልም ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።


የእነዚህን ሥጋ አትበሉም፥ በድናቸውንም አትነኩም፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements