Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 11:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 “ለምግብነት ከምታውሉት እንስሳ የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “ ‘እንድትበሉ ከተፈቀደላችሁ እንስሳት አንዱ ቢሞት፣ በድኑን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “ከሚበሉትም ቢሆን ማናቸውም እንስሳ ቢሞት የሚነካው ሁሉ እስከ ምሽት ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 “ለመ​ብል ከሚ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ እን​ስ​ሳት የሞተ ቢኖር፥ በድ​ኑን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ለመብል ከሚሆኑላችሁ እንስሶች የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 11:39
18 Cross References  

በተንጣለለው ሜዳ በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማናቸውም ሰው ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።


“የሞተውን የማናቸውንም ሰው በድን የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤


ፈሳሽ ነገር ያለበትን ሰው ገላውን የሚነካ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


መኝታውንም የሚነካ ማንም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ መካከል በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሆኑት እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


በድናቸውንም የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነርሱም በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።


“በእነዚህም የረከሳችሁ ትሆናላችሁ፤ የእነርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስበትና ከላዩም በድናቸው ቢወድቅበት፥ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።


ከአሮን ዘር ማናቸውም ሰው የለምጽ ደዌ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት፥ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሱት ነገሮች አይብላ። በበድን፥ ወይም ዘሩ በሚፈስስበት ሰው የረከሰውን ነገር የሚነካ፥


በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የገደለውን አይብላ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’


በተዘጋበትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።


ወደ ዐዛዜል የሄደውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል።


የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።


እንዲህ ያሉትን ሁሉ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውኃ ካልታጠበ ከተቀደሰው አይብላ።


ካህኑም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል፤ ካህኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል።


እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements