Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 11:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ከበድናቸውም የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰበር፤ ርኩሶች ናቸው፤ በእናንተም ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከበድናቸው አንዱ የወደቀበት ነገር ሁሉ ይረክሳል፤ ምድጃም ይሁን ማሰሮ ይሰበር፤ ርኩሳን ናቸው፤ እናንተም ተጸየፏቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ማንኛውም በድን የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ርኩስ ስለ ሆነ፥ ተጸየፉት፤ ክፍት ምድጃም ሆነ ዝግ ምድጃ ይሰበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ከእ​ነ​ዚ​ህም በድን የሚ​ወ​ድ​ቅ​በት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰ​ባ​በ​ራል፤ ርኩ​ሳን ናቸ​ውና፤ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ይሆ​ናሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ከእነዚህም በድን የሚወድቅበት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰባበራል፤ ርኩሶች ናቸው፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 11:35
8 Cross References  

ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን የሸክላ ዕቃ ይሰብሩታል፤ የእንጨቱም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይታጠባል።


ከእነርሱም አንዱ በማናቸውም የሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፥ በውስጡ ያለው ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እናንተም ዕቃውን ትሰብሩታላችሁ።


የሚቀቀልበትም ሸክላ ይሰበራል፤ ነገር ግን በናስ ዕቃ የተቀቀለ እንደሆነ ይፈገፈጋል፥ በውኃም ይለቀለቃል።


እንዲህ ካለው ዕቃ ውኃ ፈስሶ የሚበላን ምግብ ሁሉ ከነካ ምግቡ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲህም ካለው ዕቃ ሁሉ ማናቸውም የሚጠጣ መጠጥ በውስጡ ካለ እርሱ ርኩስ ይሆናል።


ነገር ግን ምንጭና የውኃ ማጠራቀምያ ጉድጓድ ንጹሕ ይሆናሉ፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ይሆናል።


ተራራውን እንደ መሰማርያው ይቃኘዋል፥ ለምለሙንም ሣር በሙሉ ይፈልጋል።


ልብሱን ያቃጥል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ወይም ከተለፋው ቆዳ የሆነ ማናቸውም ደዌው ያለበት ነገር ላይ ቢሆን፥ እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነውና በእሳት ይቃጠል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements