Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 11:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እንዲህ ካለው ዕቃ ውኃ ፈስሶ የሚበላን ምግብ ሁሉ ከነካ ምግቡ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲህም ካለው ዕቃ ሁሉ ማናቸውም የሚጠጣ መጠጥ በውስጡ ካለ እርሱ ርኩስ ይሆናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ማንኛውም ምግብ እንዲህ ካለው ዕቃ ውሃ ቢፈስስበት ይረክሳል፤ ከዚህ ዕቃ የሚጠጣውም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 የሚበላ ምግብ ሁሉ ከሸክላው ዕቃ የውሃ ነጠብጣብ ቢያርፍበት፥ ርኩስ ይሆናል፤ የሚጠጣም ነገር ቢሆን በዚያ ሸክላ ዕቃ ውስጥ ካለ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በእ​ርሱ ውስጥ ያለው፤ ውኃም የሚ​ፈ​ስ​ስ​በት፥ የሚ​በላ መብል ሁሉ ርኩስ ነው፤ በዚ​ህም ዕቃ ሁሉ ያለው የሚ​ጠጣ መጠጥ ሁሉ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 በእርሱ ውስጥ ያለው፥ ውኃም የሚፈስስበት የሚበላ መብል ሁሉ ርኩስ ነው፤ በዚህም ዕቃ ሁሉ ያለው የሚጠጣ መጠጥ ሁሉ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 11:34
7 Cross References  

ለንጹሖች ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ነገር ምንም የለም፤ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው ረክሶአል።


ሀብቱን በአራጣ ብዛትና በቅሚያ የሚያበዛ ለድሀ ለሚራራ ያከማችለታል።


የክፉዎች መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፥ ይልቁንም በክፉ አሳብ ሲያቀርቡት አስጸያፊ ነው።


ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኀጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው።


የኀጥኣን መሥዋዕት በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ከእነርሱም አንዱ በማናቸውም የሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፥ በውስጡ ያለው ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እናንተም ዕቃውን ትሰብሩታላችሁ።


ከበድናቸውም የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰበር፤ ርኩሶች ናቸው፤ በእናንተም ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements