Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ከእነርሱም አንዱ በማናቸውም የሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፥ በውስጡ ያለው ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እናንተም ዕቃውን ትሰብሩታላችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በድኑም በሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፣ በውስጡ ያለ ነገር ሁሉ ርኩስ ስለሚሆን ዕቃውን ስበሩት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ከነርሱ የአንዳቸው በድን በሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፥ በዕቃው ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ስለሚረክስ፥ ሸክላውን ስበሩት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳች በው​ስጡ የወ​ደ​ቀ​በ​ትን የሸ​ክ​ላ​ውን ዕቃ ሁሉ ስበ​ሩት፤ በው​ስ​ጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ከእነርሱም አንዳች በውስጡ የወደቀበትን የሸክላውን ዕቃ ሁሉ ስበሩት፥ በውስጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 11:33
11 Cross References  

ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን የሸክላ ዕቃ ይሰብሩታል፤ የእንጨቱም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይታጠባል።


የሚቀቀልበትም ሸክላ ይሰበራል፤ ነገር ግን በናስ ዕቃ የተቀቀለ እንደሆነ ይፈገፈጋል፥ በውኃም ይለቀለቃል።


እርሱም ደግሞ ለራሱ ሁሉን ነገር በሥሩ ለማስገዛት በሚችልበት ኃይሉ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።


ሞዓብን ማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ሰብሬዋለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል ጌታ።


ቤቱንም፥ ድንጋዮቹንም፥ እንጨቱንም፥ የቤቱንም ምርጊት ሁሉ ያፈርሳል፤ እነርሱንም ከከተማው ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወጣል።


ከበድናቸውም የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰበር፤ ርኩሶች ናቸው፤ በእናንተም ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ።


እንዲህ ካለው ዕቃ ውኃ ፈስሶ የሚበላን ምግብ ሁሉ ከነካ ምግቡ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲህም ካለው ዕቃ ሁሉ ማናቸውም የሚጠጣ መጠጥ በውስጡ ካለ እርሱ ርኩስ ይሆናል።


ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ይዘጋጃል፤ ደኅና ተደርጎ ከተለወሰ በኋላ ታመጣዋለህ፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የተጋገረውን የእህል ቁርባን ቈራርሰህ ታቀርበዋለህ።


ልብሱን ያቃጥል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ወይም ከተለፋው ቆዳ የሆነ ማናቸውም ደዌው ያለበት ነገር ላይ ቢሆን፥ እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነውና በእሳት ይቃጠል።


መክደኛው ያልታሰረ የተከፈተ ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements