Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 11:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “በአራት እግሮች የሚንቀሳቀሱ፥ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ ‘ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ክንፍ ያላቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ የረከሱ ናቸው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “የሚ​በ​ር​ርም፥ በአ​ራት እግ​ሮ​ችም የሚ​ሄድ ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የሚበርርም፥ በአራት እግሮችም የሚሄድ ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 11:20
14 Cross References  

እነዚህ መለያየትን የሚፈጥሩ ፍጥረታውያን የሆኑ፥ መንፈስም የሌላቸው ናቸው።


እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፤ አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች በደመ ነፍስ በሚያውቁት ነገር ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።


ዴማስ የአሁንዋን ይህችን ዓለም ወድዶ ትቶኛል፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል። ቀርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”


አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


ክንፍ ያላቸው ጥቃቅን ነፍሳት ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው፤ እነርሱን አትብሏቸው።


በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ መካከል፥ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ነገር ግን ሌሎች አራት እግሮች ያሉአቸው ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።


ጴጥሮስ ግን “ጌታ ሆይ! አይሆንም፤ አንዳች ርኩስ የሚያስጸይፍም ከቶ በልቼ አላውቅምና፤” አለ።


ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጁላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ።


ነገር ግን ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው፥ በአራት እግሮች ከሚሄዱ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት እነዚህን ትበላላችሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements