Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 10:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አሮንም ሙሴን፦ “እነሆ፥ ዛሬ የኃጢአታቸውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውን በጌታ ፊት አቀረቡ፤ ሆኖም ይህ ሁሉ ነገር በእኔ ላይ ደረሰብኝ፤ ዛሬስ የኃጢአት መሥዋዕት ብበላ ኖሮ በጌታ ፊት መልካም ይሆን ነበርን?” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አሮንም ሙሴን፣ “እነሆ፤ በዛሬው ቀን የኀጢአት መሥዋዕታቸውንና የሚቃጠል መሥዋዕታቸውን በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፤ እኔም እንዲህ ያለ ነገር የደረሰብኝ ሰው ነኝ፤ ታዲያ፣ ዛሬ የኀጢአት መሥዋዕቱን ብበላ ኖሮ እግዚአብሔርስ ደስ ይለው ኖሯልን?” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አሮንም “ስለ ኃጢአት ስርየት የቀረበውን መሥዋዕት ዛሬ በልቼው ቢሆን ኖሮ ለካ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኝ ኖሮአልን? እነሆ ሕዝቡ ዛሬ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አምጥተዋል፤ ነገር ግን እነዚህ እንደዚህ ያሉ ነገሮች በእኔ ላይ ደረሱ” ሲል መለሰ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አሮ​ንም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ ዛሬ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በለዩ ጊዜ፥ ይህች አገ​ኘ​ችኝ፤ ዛሬም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት እበላ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም አይ​ደ​ለም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አሮንም ሙሴን፦ እነሆ ዛሬ የኃጢያታቸውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕታቸውን በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፤ ይህም ሁሉ ደረሰብኝ፤ ዛሬስ የኃጢያት መሥዋዕት በበላሁ ኖሮ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ኖሮአልን? አለው።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 10:19
17 Cross References  

የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው።


አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ።


ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል፤ እግዚአብሔር ቁርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኅዘንም ትከድናላችሁ።


“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።


“በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ መካከል በሮችን የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። ቁርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም።


ለጌታም የወይን ጠጅን ቁርባን አያፈስሱም፥ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘን እንጀራም ይሆንባቸዋል፥ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ፤ እንጀራቸውም ለሆዳቸው ይሆናል እንጂ ወደ ጌታ ቤት አይገባም።


በጾሙ ጊዜ ልመናቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፤ ይልቁንም በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ” አለኝ።


ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም አገር የከበረውንም ዘይት ታመጡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፥ ሌላ መሥዋዕታችሁም ደስ አያሰኘኝም።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


በዚህ መንገድ ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ እያለች ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል።


እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።


ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፤ ደስ ይበላችሁ።


“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?” ይላል ጌታ። የሚቃጠለውን የአውራ በግና የሰቡ እንስሳትን ስብ ጠግቤአለሁ፤ በበሬ፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስ አልሰኝም።


በኀዘኔም ጊዜ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ወይም ንጹህ ባልነበርኩ ጊዜ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት መባ የለም፤ ለአምላኬ ጌታ ድምጽ ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።


በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”


ሙሴም ሰማ በፊቱም መልካም ሆነ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements