Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ነገር ግን የሚወዘወዘውን ፍርምባ፥ የሚነሣውንም ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶች ልጆችህና ሴቶች ልጆችህም በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ፤ እነዚህ ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕት ለአንተና ለልጆችህ ድርሻ እንዲሆኑ የተሰጡ ናቸውና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የእናንተ ድርሻ ሆኖ ስለ ተሰጠ፣ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ በሆነ ስፍራ ብሉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነገር ግን በመወዝወዝ ልዩ መባ ሆኖ ለእግዚአብሔር ከቀረበ በኋላ የካህናቱ ድርሻ እንዲሆን ስለ ተፈቀደ ፍርምባውንና ወርቹን አንተና ቤተሰብህ ሴቶች ልጆችህ ጭምር ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም በተቀደሰ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህም የእስራኤል ሕዝብ የአንድነት መሥዋዕት አድርገው ከሚያቀርቡት መባ ሁሉ ተከፍሎ ለአንተና ለልጆችህ ተሰጥቶአል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነ​ዚ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ፍር​ም​ባና ወርች አንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ልጆ​ችህ፥ ቤተ​ሰ​ብ​ህም ተለ​ይቶ በን​ጹሕ ስፍራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነዚህም ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕቶች ለአንተና ለልጆችህ ሥርዓት እንዲሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የሚወዘወዘውን ፍርምባ፥ የሚነሣውንም ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋርም ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህም በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 10:14
10 Cross References  

ይህም ደግሞ ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ የሚያቀርቡትን የመወዝወዝ ቁርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ ማድረግ፥ ሥራውንም መፈጸም ነው።


ሙሴም እንደ ታዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘ።


በእነሱ እጃቸው ሙሉ እንዲሆንና የተቀደሱ እንዲሆኑ ማስተስረያ የሆነውን ነገር ይብሉት፤ የተቀደሰ ስለሆነ ሌላ ሰው አይብላው።


ለጌታም ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ለአንተም ለልጆችህም የተሰጠ ድርሻ ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም እንዲህ ታዝዣለሁና።


የእስራኤልም ልጆች ለካህኑ የሚያቀርቡትን ማናቸውም የተቀደሱ ነገሮች ስጦታ ሁሉ ለእርሱ ይሆናሉ።


እንዲህም አለኝ፦ በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ ጌታ የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቁርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ።


የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ማናቸውም ምእመን ግን ከእርሱ አይብላ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements