ዘሌዋውያን 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፤ ራሱንም ይቈለምመዋል፤ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል። ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፈጠፋል፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ካህኑም ወደ መሠዊያው ያምጣው፤ ራሱን ቈልምሞ ይቀንጥሰው፤ የተቈረጠውንም ራስ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፍጠፍ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ካህኑም ይህን ወፍ ተቀብሎ ወደ መሠዊያው በማቅረብ አንገቱን ይቈልምመው፤ በመሠዊያውም ላይ በሚገኘው እሳት ያቃጥለው፤ ደሙም በመሠዊያው ጐን ይንጠፍጠፍ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፤ አንገቱንም ይቈርጠዋል፥ በመሠዊያውም ላይ ያኖረዋል። ደሙንም በመሠዊያው አጠገብ ያንጠፈጥፈዋል፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፥ ራሱንም ይቈለምመዋል፥ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል። ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፈጠፋል፤ See the chapter |