ሰቈቃወ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ርኩሰቷ በቀሚሷ ላይ ታየ፤ ወደ ፊት የሚሆንባትን አላሰበችም፤ አወዳደቋ አስደንጋጭ ሆነ፤ የሚያጽናናትም አልነበረም፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ መከራዬን ተመልከት፤ ጠላት ድል አድርጓልና!” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አደፍዋ በቀሚስዋ ላይ ይታያል፤ ለወደፊት ምን እንደሚደርስባት አላሰበችም፤ አወዳደቅዋ የሚያሰቅቅ ነው፤ የሚያጽናናት ከቶ የለም፤ ጠላቶችዋ ድል ስላደረግዋት፥ መከራዋን እንዲመለከትላት ወደ እግዚአብሔር ጸለየች። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ጤት። ግዳጅዋ ከእግርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ ከባድ ሸክምን ተሸከመች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት። See the chapter |