ሰቈቃወ 1:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና። ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኃጢአቴ ሁሉ እንዳደረግህብኝ አድርግባቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 “ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ ከኀጢአቴ ሁሉ የተነሣ፣ በእኔ ላይ እንዳደረግህብኝ፣ በእነርሱም ላይ አድርግባቸው፤ የሥቃይ ልቅሶዬ በዝቷል፤ ልቤም ደክሟል።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 “ ክፉ ሥራቸውን ሁሉ ተመልከት፤ በበደሎቼ ሁሉ ምክንያት በእኔ ላይ እንዳደረግኸው በእነርሱም ላይ አድርግ ዘወትር ስለምቃትት ልቤ እየደከመብኝ ነው።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፥ ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኀጢአቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረምኸኝ እነርሱን ቃርማቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና። ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኃጢአቴ ሁሉ እንዳደረግህብኝ አድርግባቸው። See the chapter |