ሰቈቃወ 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እየጮኹ ያለቅሳሉ እንጀራም ይፈልጋሉ፥ ሰውነታቸውን ለማበርታት የከበረ ሀብታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፥ አቤቱ፥ ተጐሳቁያለሁና እይ፥ ተመልከትም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እንጀራ በመፈለግ፣ ሕዝቧ ሁሉ በሥቃይ ይጮኻል፤ በሕይወት ለመኖር፣ የከበረ ሀብታቸውን በምግብ ይለውጣሉ፤ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ ተመልከተኝም፤ እኔ ተዋርጃለሁና።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ሕዝብዋ ምግብ ማግኘት ፈልገው ይቃትታሉ፤ በሕይወት ለመኖር ሲሉ ሀብታቸውን ሁሉ በምግብ ይለውጣሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ “እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከተን! ውርደታችንን ሁሉ እይልን!” እያሉ ይጮኻሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እንጀራ አጥተው ያለቅሳሉ፤ ሰውነታቸውን ለማበርታት ፍላጎታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፤ አቤቱ! ተጐሳቍያለሁና እይ፤ ተመልከትም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እየጮኹ ያለቅሳሉ እንጀራም ይፈልጋሉ፥ ሰውነታቸውን ለማበርታት የከበረ ሀብታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፥ አቤቱ፥ ተጐሳቍያለሁና እይ፥ ተመልከትም። See the chapter |