መሳፍንት 9:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)44 ከዚያም አቤሜሌክና አብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማይቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፥ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም44 ከዚያም አቢሜሌክና ዐብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፣ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም44 አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የተመደበው ቡድን የከተማይቱን ቅጽር በር ለመጠበቅ ተጣድፈው ወጥተው በከተማው መግቢያ በር ላይ ቆሙ፤ የቀሩት ሁለቱ ቡድኖች በመስኩ በተገኙት ላይ አደጋ ጥለው ፈጁአቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)44 አቤሜሌክም ከእርሱም ጋር ያሉት ሠራዊት በከተማዪቱ መግቢያ በር ሸምቀው ቆሙ። እነዚያ ሁለቱ ሠራዊት ግን ወደ ጫካው ተበትነው አጠፉአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)44 አቤሜሌክም ከእርሱም ጋር ያሉት ወገኖች ተጣደፉ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሙ፥ ሁለቱም ወገኖች በእርሻው ውስጥ በነበሩት ሁሉ ላይ ሮጡባቸው፥ መቱአቸውም። See the chapter |