መሳፍንት 9:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 የሴኬም ነዋሪዎችም አቤሜሌክን ሸምቀው የሚጠባበቁትን ሰዎች መደቡ፤ ሰዎቹም እርሱን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በዚያ የሚያልፈውን ሁሉ ዘረፉ፤ ወሬውም ለአቤሜሌክ ደረሰው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 የሴኬም ገዦችም አቢሜሌክን ሸምቀው የሚጠባበቁትን ሰዎች መደቡ፤ ሰዎቹም እርሱን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በዚያ የሚያልፈውን ሁሉ ዘረፉ፤ ወሬውም ለአቢሜሌክ ደረሰው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 የሴኬም ኗሪዎች በአቤሜሌክ ላይ በጠላትነት ተነሥተው ጥቂት ሰዎችን መርጠው በተራሮች ጫፍ ላይ ሸመቁ፤ በመንገዳቸው የሚያልፈውን ሰው ሁሉ ዘረፉ፤ አቤሜሌክም ይህን ሁሉ ሰማ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 የሰቂማም ሰዎች በተራሮች ራስ ላይ ድብቅ ጦር አደረጉ፤ መንገድ ተላላፊዎችንም ሁሉ ይዘርፉ ነበር፤ ለአቤሜሌክም ይህን አወሩለት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 የሴኬምም ሰዎች በተራሮች ራስ ላይ ድብቅ ጦር አደረጉ፥ መንገድ ተላላፊዎችንም ሁሉ ይዘርፉ ነበር፥ አቤሜሌክም ይህን ወሬ ሰማ። See the chapter |