Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እንግዲህ ዛሬ በይሩበኣልና በቤተሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና በቅንነት ከሆነ እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንግዲህ ዛሬ በይሩባኣልና በቤተ ሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና ያለ እንከን ከሆነ እናንተ በአቢሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው!

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እንግዲህ ዛሬ ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ ያደረጋችኹት በቅንነትና ተገቢ በሆነ መንገድ ከሆነ ከአቤሜሌክ ጋር ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ደስ ይበለው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለይ​ሩ​በ​ኣ​ልና ለቤቱ እው​ነ​ት​ንና ቅን​ነ​ትን ዛሬ አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ፤ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እር​ሱም ደግሞ በእ​ና​ንተ ደስ ይበ​ለው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እንግዲህ ለይሩበኣልና ለቤቱ እውነትንና ቅንነትን ዛሬ አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፥ እርሱ ደግሞ በእናንተ ደስ ይበለው፥

See the chapter Copy




መሳፍንት 9:19
6 Cross References  

“ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰውን የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፤ በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና።


እናንተ ግን በእብሪታችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲህ ያለው ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።


እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን በእውነትም ከተገረዙት ወገን የሆንን ነንና።


ስለዚህም፥ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፥ “ይሩበኣል” ብለው ጠሩት።


ነገር ግን እናንተ ዛሬ በአባቴ ቤተሰብ ላይ ዐመፃችሁ፤ ሰባ ልጆቹን በአንዲት ድንጋይ ላይ ዐረዳችሁ፤ ዘመዳችሁ ስለ ሆነም አባቴ ከባርያው የወለደውን ልጅ አቤሜሌክን በሴኬም ነዋሪዎች ላይ አነገሣችሁት።


ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements