Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ነገር ግን እናንተ ዛሬ በአባቴ ቤተሰብ ላይ ዐመፃችሁ፤ ሰባ ልጆቹን በአንዲት ድንጋይ ላይ ዐረዳችሁ፤ ዘመዳችሁ ስለ ሆነም አባቴ ከባርያው የወለደውን ልጅ አቤሜሌክን በሴኬም ነዋሪዎች ላይ አነገሣችሁት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ነገር ግን እናንተ ዛሬ በአባቴ ቤተ ሰብ ላይ ዐመፃችሁ፤ ሰባ ልጆቹን በአንዲት ድንጋይ ላይ ዐረዳችሁ፤ ዘመዳችሁ ስለ ሆነም አባቴ ከባሪያው የወለደውን ልጅ አቢሜሌክን በሴኬም ገዦች ላይ አነገሣችሁት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዛሬ ግን እናንተ በአባቴ ቤተሰብ ላይ በጠላትነት ተነሣችሁ፤ ልጆቹን ገደላችሁ፤ ሰባውንም በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳችሁ፤ ይህንንም ያደረጋችኹት ጌዴዎን ከገረዱ የወለደው አቤሜሌክ የእናንተ ዘመድ ስለ ሆነ ነው፤ እርሱንም የሴኬም ንጉሥ አደረጋችሁት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እና​ን​ተም ዛሬ በአ​ባቴ ቤት ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን ልጆ​ቹ​ንም በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገድ​ላ​ች​ኋል፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁም ስለ​ሆነ የዕ​ቅ​ብ​ቱን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን በሰ​ቂማ ሰዎች ላይ አን​ግ​ሣ​ች​ኋል፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እናንተም ዛሬ በአባቴ ቤት ተነሥታችኋልና፥ ሰባ የሆኑትን ልጆቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ አርዳችኋልና፥ ወንድማችሁም ስለ ሆነ የባሪያይቱን ልጅ አቤሜሌክን በሴኬም ሰዎች ላይ አንግሣችኋልና፥

See the chapter Copy




መሳፍንት 9:18
8 Cross References  

በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።


በመጨረሻም ዛፎቹ በሙሉ የእሾኽ ቊጥቋጦን፥ “መጥተህ ንጉሣችን ሁን” አሉት።


እንዲሁም ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን ያደረገላቸውን በጎ ነገር ሁሉ አስበው ለቤተ ሰቡ ውለታ መላሽ ሆነው አልተገኙም።


“የሴኬምን ነዋሪዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፤ ‘ሰባዎቹ የይሩባኣል ልጆች ቢገዟችሁ ይሻላል ወይስ አንድ ሰው ብቻ?’ የሥጋችሁ ቁራጭ፥ ያጥንታችሁ ፍላጭ መሆኔን ልብ በሉ።”


አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፥ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን አሰባችሁ ማለት ነው።


እንግዲህ ዛሬ በይሩበኣልና በቤተሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና በቅንነት ከሆነ እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው


Follow us:

Advertisements


Advertisements