Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “እንግዲህ አቤሜሌክን ስታነግሡት በቅንነትና በእውነት አድርጋችሁት ከሆነ፥ ይሩበኣልንና ቤተሰቡን በበጎ ዐይን ተመልክታችሁ ላደረገው የሚገባውን አይታችሁለት ከሆነ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “እንግዲህ አቢሜሌክን ስታነግሡት በእውነትና ያለ እንከን አድርጋችሁት ከሆነ፣ ይሩባኣልንና ቤተ ሰቡን በበጎ ዐይን ተመልክታችሁ ላደረገው የሚገባውን አይታችሁለት ከሆነ፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ኢዮአታምም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አላቸው፤ “አቤሜሌክን ስታነግሡ በቅንነትና ተገቢ በሆነ መንገድ ነውን? ጌዴዎን ያደረገውን በማስታወስ ቤተሰቡን እንደሚገባ ረዳችሁለትን?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አሁን እን​ግ​ዲህ አቤ​ሜ​ሌ​ክን በማ​ን​ገ​ሣ​ችሁ እው​ነ​ት​ንና ቅን​ነ​ትን አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ፥ ለይ​ሩ​በ​ኣ​ልም፥ ለቤ​ቱም በጎ አድ​ር​ጋ​ችሁ እን​ደ​ሆ​ነና እንደ እጁም ዋጋ መጠን ለእ​ርሱ የተ​ገ​ባ​ውን አድ​ር​ጋ​ችሁ እንደ ሆነ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አሁን እንግዲህ አቤሜሌክን በማንገሣችሁ እውነትንና ቅንነትን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ ለይሩበኣልም ለቤቱም በጎ አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ እንዳደረገውም መጠን ለእርሱ የተገባውን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥

See the chapter Copy




መሳፍንት 9:16
4 Cross References  

እንዲሁም ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን ያደረገላቸውን በጎ ነገር ሁሉ አስበው ለቤተ ሰቡ ውለታ መላሽ ሆነው አልተገኙም።


ስለዚህም፥ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፥ “ይሩበኣል” ብለው ጠሩት።


የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።


አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፥ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን አሰባችሁ ማለት ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements