Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከዚያም የበኲር ልጁ ወደ ሆነው ዮቴር ዘወር ብሎ፥ “ግደላቸው” አለው፤ ዮቴር ግን ትንሽ ልጅ ነበርና ስለ ፈራ ሰይፉን አልመዘዘም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም ወደ በኵር ልጁ ወደ ዮቴር ዘወር ብሎ፣ “ግደላቸው” አለው፤ ዮቴር ግን ትንሽ ልጅ ነበርና ስለ ፈራ ሰይፉን አልመዘዘም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህ በኋላ የበኲር ልጁን ዬቴርን “በል አሁን ግደላቸው!” ብሎ አዘዘው። ልጁ ግን ሰይፉን ሳይመዝ ቀረ፤ ገና ልጅ ስለ ነበር አመነታ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በኵ​ሩ​ንም ዮቶ​ርን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ግደ​ላ​ቸው” አለው፤ ብላ​ቴ​ናው ግን ገና ትንሽ ነበ​ረና ስለ ፈራ ሰይ​ፉን አል​መ​ዘ​ዘም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በኩሩንም ዬቴርን፦ ተነሥተህ ግደላቸው አለው፥ ብላቴናው ግን ገና ብላቴና ነበረና ስለ ፈራ ሰይፉን አልመዘዘም።

See the chapter Copy




መሳፍንት 8:20
5 Cross References  

የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።


ሳሙኤልም፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በጌታ ፊት ቆራረጠው።


እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎቹን የጦር አዛዦች እንዲህ አላቸው፦ “ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ።” ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።


ጌዴዎንም፥ “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ናቸው፤ ባትገድሏቸው ኖሮ እኔም እንደማልገድላችሁ በሕያው ጌታ ስም አረጋግጥላችሁ ነበር” ብሎ መለሰላቸው።


ዜባሕና ጻልሙናም፥ “የሰው ጉልበቱ እንደ ሰውነቱ መጠን ነውና፥ አንተው ራስህ ግደለን አሉት፤” ጌዴዎንም ተነሥቶ ገደላቸው፤ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበሩትንም ጌጦች ወሰደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements