Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሚሉትንም አድምጥ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሚሉትንም ስማ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ።” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም አድ​ም​ጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ እጆ​ችህ ይበ​ረ​ታሉ፤ ወደ ሰፈ​ርም ትወ​ር​ዳ​ለህ” አለው። እር​ሱም ከሎ​ሌው ፋራን ጋር ከሰ​ፈሩ በአ​ንድ ወገን የአ​ምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈ​ረ​በት ወረደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የሚናገሩትንም ትሰማለህ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትወርድ ዘንድ እጅህ ትበረታለች አለው። እርሱና ሎሌው ፉራ በሰፈሩ ዳርቻ ወደ ነበሩት ሰልፈኞች ወረዱ።

See the chapter Copy




መሳፍንት 7:11
15 Cross References  

በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ።


ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።


ጌታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና፥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤትም ለመሥራት እጃቸውን እንዲያጸኑ የአሦርን ንጉሥ ልብ ወደ እነርሱ መልሶአልና የቂጣውን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አከበሩ።


የሳኦል ልጅ ዮናታንም ዳዊት ወዳለበት ወደ ሖሬሽ ሄዶ፥ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው፤


ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን ዞረው በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መንገድ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብጽ ምድር ለጦርነት ተሰልፈው ወጡ።


ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርሷም አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፥ እርሷ ለባርያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፥ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”


እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን፥ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ እጸልያለሁ፤


ሁሉም እንዲህ እያሉ አስፈራሩን፦ “ከሥራው እጃቸውን ያላላሉ፥ አይሠራምም” አሁንም እጄን አበርታ።


የፍልስጥኤም ጦር ሰፈር ሰዎችም፥ “ኑ ወደ እኛ ውጡ፤ የምናሳያችሁ ነገር ይኖራል” ሲሉ በዮናታንና በጋሻ ጃግሬው ላይ ጮኹባቸው። ስለዚህ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “ተከትለኸኝ ውጣ፤ ጌታ በእስራኤላውያን እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና” አለው።


አደጋ ለመጣል የምትፈራ ከሆነ ግን፥ ፉራ ከተባለው አገልጋይህ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤


ዳዊትም ሒታዊውን አቢሜሌክንና የጸሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ሰፈር አብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፥ “እኔ አብሬህ እወርዳለሁ” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements