Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 6:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር እንደጠየቀው አደረገ፤ ባዘቶው ብቻ ደረቅ ሲሆን፥ ምድሩ በሙሉ በጤዛ ተሸፍኖ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር እንደ ተጠየቀው አደረገ፤ ምድሩ በሙሉ በጤዛ ሲሸፈን፣ ባዘቶው ብቻ ደረቅ ሆነ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ያንኑ ምልክት አደረገ፤ በማግስቱ ጧት የጠጒሩ ባዘቶ ደረቅ ሆኖ በዙሪያው ያለው መሬት ግን በጤዛ ርሶ ተገኘ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ሌሊት እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ሆነ፥ በም​ድ​ሩም ሁሉ ላይ ጠል ወረደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት እንዲሁ አደረገ፥ በጠጉሩ ብቻ ላይ ደረቅ ነበረ፥ በምድሩም ሁሉ ላይ ጠል ነበረ።

See the chapter Copy




መሳፍንት 6:40
3 Cross References  

ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደገና ልጠይቅ። በጠጉሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።”


ይሩበኣል የተባለው ጌዴዎን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጠዋት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተ ሰሜን በኩል፥ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።


‘ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከጌታ ከአምላክህ ለምን።’


Follow us:

Advertisements


Advertisements