Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 6:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የጌታ መልአክ፥ “ሥጋውን እርሾ ያልገባበትን ቂጣ ወስደህ፥ በዚያ ዐለት ላይ አኑር፤ መረቁንም በሥጋውና በቂጣው ላይ አፍስስ” አለው፤ ጌዴዎንም እንደ ታዘዘው አደረገ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የእግዚአብሔር መልአክ፣ “ሥጋውንና ቂጣውን ወስደህ፣ በዚያ ዐለት ላይ አኑር፤ መረቁንም በሥጋውና በቂጣው ላይ አፍስስ” አለው፤ ጌዴዎንም እንደ ታዘዘው አደረገ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 መልአኩም “ሥጋውንና እንጀራውን በዚህ አለት ላይ አስቀምጠህ መረቁን በላዩ አፍስስበት” ሲል አዘዘው፤ ጌዴዎንም እንደታዘዘው አደረገ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ሥጋ​ው​ንና የቂ​ጣ​ውን እን​ጎቻ ወስ​ደህ በዚህ ድን​ጋይ ላይ አኑር፤ መረ​ቁ​ንም አፍ​ስስ” አለው። እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የእግዚአብሔርም መልአክ፦ ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ ወስደህ በዚህ ድንጋይ ላይ አኑር፥ መረቁንም አፍስስ አለው። እንዲሁም አደረገ።

See the chapter Copy




መሳፍንት 6:20
7 Cross References  

ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቁርባኑ ጋር ወስዶ በዐለት ላይ ለጌታ ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ ጌታ አስደናቂ ነገር አደረገ፤


ጌዴዎን ወደ ቤቱ ሄደ፤ የፍየል ጠቦትም ዐረደ፤ አንድ ኢፍ መስፈሪያ ዱቄት ወስዶ እርሾ ያልገባበት ቂጣ ጋገረ። ሥጋውን በቅርጫት፥ መረቁን በምንቸት ይዞ በመምጣት በባሉጥ ሥር ለተቀመጠው አቀረበለት።


መልአኩም በያዘው በትር ጫፍ ሥጋውንና ቂጣውን ነካ፤ ከዐለቱም እሳት ወጥቶ ሥጋውንና ቂጣውን በላ፤ ከዚያም የጌታ መልአክ ተሰወረ።


የጌታም መልአክ፥ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለጌታ አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የጌታ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር።


“አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፥


ከዚያም ማኑሄ የጌታን መልአክ “የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements