Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ ጌታን አመስግኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣ ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 መሪዎች እስራኤልን ስለ መሩ፥ ሕዝቡም በፈቃደኛነት ራሱን ስላቀረበ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ!

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ መሳ​ፍ​ንት ስለ መሩ ሕዝ​ቡም ስለ ፈቀዱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።

See the chapter Copy




መሳፍንት 5:2
23 Cross References  

ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ነው፥ በሕዝቡ መካከል ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ወደ ሰጡት፥ ጌታን አመስግኑ።


ግርማዊ ክብር ከልደትህ ጊዜ አንሥቶ፥ የተቀደሰ ሞገስም ከማኅጸን፥ የወጣትነትም ጠል የአንተ ነው።


ከእርሱም በኋላ በፈቃዱ ራሱን ለጌታ የቀደሰ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።


በጎ ፈቃዱን እንድትፈልጉና እንድታደርጉ ሁለቱንም በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።


ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና፤ በዝሙትዋ ምድርን ያበላሸችውን ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባት፥ የባርያዎቹንም ደም ከእጅዋ ተበቀሎአልና።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


ነገር ግን በጎነትህ በፈቃድህ እንጂ በግድ እንዳይሆን፥ ሳልማከርህ ምንም ነገር ላደርግ አልፈልግሁም።


እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና፥ እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበው ይስጥ፤ በኀዘን ወይም በግድ ግን አይሁን።


በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።


ይህን በፈቃዴ ባደርገው ዋጋ አለኝና፤ ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል።


ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፥


እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው። የበቀል አምላክ ተገለጠ።


አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ ምስጋናህም እንዲሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው፥ ቀኝህ ጽድቅን የተሞላች ናት።


ጌታ ሕያው ነው፥ አምላኬም መጠጊያዬ ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።


ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በፈቃደኝነት ራሳቸውን የሰጡትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።


“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”


በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፥ ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፥ የጌታንም ጽድቅ፥ ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።”


ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥ ውለታውንም ከቶ አትርሺ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements