መሳፍንት 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ዲቦራ መልሳ፥ “ይሁን እሺ፤ መሄዱን አብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ ጌታ ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ዲቦራ መልሳ፣ “ይሁን ዕሺ፤ መሄዱን ዐብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባርቅ ጋራ ወደ ቃዴስ ሄደች፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እርስዋም “እሺ፥ እኔም ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ስለሚሰጥ ድሉ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው፤ ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ዘመተች። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ዲቦራም፥ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና በዚህ በምትሄድበት መንገድ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው። ዲቦራም ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እርሷም፦ በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና በዚህ በምትሄድበት መንገድ ለአንተ ክብር አይሆንም አለችው። ዲቦራም ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች። See the chapter |