መሳፍንት 4:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 የሔቤር ሚስት ኢያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፣ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፣ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋራ ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ሲሣራ በጣም ደክሞት ስለ ነበር ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ ከዚህ በኋላ የሔቤር ሚስት ያዔል መዶሻና የድንኳን ካስማ ወስዳ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ካስማውንም በጆሮ ግንዱ ጠልቆ መሬት እስኪነካ ድረስ ቸነከረችው፤ እርሱም ሞተ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 የሔቤርም ሚስት ኢያዔል የድንኳኑን ካስማ ወሰደች፤ በሁለተኛ እጅዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረበች፤ በጆሮ ግንዱም ካስማውን ቸነከረችበት፤ እርሱም ደክሞ አንቀላፍቶ ነበርና ካስማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እርሱም ከእግርዋ በታች ተንፈራፈረ፤ ተዘርሮም ሞተ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 የሔቤርም ሚስት ኢያዔል የድንኳን ካስማ ወሰደች፥ በእጅዋም መዶሻ ያዘች፥ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረበች፥ በጆሮግንዱ ካስማውን ቸነከረች፥ እርሱም ደክሞ እንቀላፍቶ ነበርና ካስማው ወደ መሬት ጠለቀ፥ እርሱም ሞተ። See the chapter |