መሳፍንት 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበ ለችውና፥ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ኢያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበለችውና፣ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ያዔልም ሲሣራን ልትቀበለው ወጥታ “ጌታዬ ና፥ ወደ ድንኳኔ ግባ፤ ከቶ አትፍራ” አለችው፤ እርሱም ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ በልብስ ሸፈነችው፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ኢያዔልም ሲሣራን ለመቀበል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አትፍራም” አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ በምንጣፍም ሸፈነችው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ኢያዔልም ሲሣራን ለመገናኘት ወጥታ፦ ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፥ አትፍራ አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፥ በመጎናጸፊያዋም ሸፈነችው። See the chapter |