መሳፍንት 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በሐጾር ንጉሥ በየቡስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደ ሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ሮጠ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በአሦር ንጉሥ በኢያቢስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ኢያዔል ድንኳን ሮጠ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 የሐጾር ንጉሥ ያቢን ከሔቤር ቤተሰብ ጋር ሰላም መሥርቶ ይኖር ስለ ነበር ሲሣራ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ገባ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ሲሣራም ወደ ጓደኛው ወደ ቄናዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያዔል ድንኳን በእግሩ ሸሸ፤ በአሶር ንጉሥ በኢያቢንና በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበርና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በአሶር ንጉሥም በኢያቢስና በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበረና ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ ወደ ቄናዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያዔል ድንኳን ደረሰ። See the chapter |