መሳፍንት 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የጌታም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ ጌታ የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሽን ሪሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሽን-ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 የእግዚአብሔር መንፈስ በርሱ ላይ ወረደ፤ የእስራኤል መስፍን ሆኖ ወደ ጦርነትም ወጣ። እግዚአብሔር የአራም ንጉሥ ኵስርስቴምን አሳልፎ ስለ ሰጠው ድል አደረገ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ፥ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፥ ለሰልፍ ወጣ፥ እግዚአብሔርም የመሰጴጦምያን ንጉሥ ኩሰርሰቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፥ እጁም በኩሰርሰቴም ላይ አሸነፈች። See the chapter |