Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 21:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሴቶች ልጆቻችንን ለእነዚህ ብንያማውያን በጋብቻ ላንሰጥ በጌታ ስለማልን ለተረፉት እንዴት ሚስት ልናገኝላቸው እንችላለን?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሴቶች ልጆቻችንን ለእነዚህ ብንያማውያን በጋብቻ ላንሰጥ በእግዚአብሔር ስለ ማልን ለተረፉት እንዴት ሚስት ልናገኝላቸው እንችላለን?”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከሴቶች ልጆቻችን ማንኛይቱንም ለእነርሱ እንዳንድር በመሐላ ቃል ስለ ገባን ከሞት የተረፉት ብንያማውያን ሚስት ያገኙ ዘንድ ምን እናድርግ?” አሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እኛ ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ዳ​ን​ድ​ር​ላ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምለ​ና​ልና የተ​ረ​ፉት ሚስ​ቶ​ችን እን​ዲ​ያ​ገኙ ምን እን​ድ​ርግ?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እኛ ልጆቻችንን እንዳንድርላቸው በእግዚአብሔር ምለናልና የተረፉት ሚስቶችን እንዲያገኙ ምን እናድርግ? አሉ።

See the chapter Copy




መሳፍንት 21:7
7 Cross References  

እስራኤላውያን በምጽጳ፥ “ከእኛ አንድም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።


ሕዝቡ ግን ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? ይህ አይሆንም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፥ ሕያው ጌታን! ከራስ ጠጉሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።


‘ልጁን ለብንያማዊ የሚድር ርጉም ይሁን’ ብለን እኛ እስራኤላውያን ስለ ተማማልን እንግዲህ ልጆቻችንን ልንድርላቸው አንችልም፤


በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ስለ ወንድሞቻቸው ስለ ብንያማውያን በማዘን እንዲህ አሉ፤ “ዛሬ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ታጥቷል፤


ከዚያም፥ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በጌታ ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከያቤሽ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤


አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፥ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements