Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የቁባቴንም ሬሳ ከቈራረጥሁ በኋላ እያንዳንዱን ቁራጭ፥ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ወዳለበት አገር ሰደድሁ፤ ይህን ያደረግሁትም ሰዎቹ በእስራኤል ዘንድ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸሙ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የቁባቴንም ሬሳ ከቈራረጥሁ በኋላ እያንዳንዱን ቍራጭ፣ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ወዳለበት አገር ሰደድሁ፤ ይህን ያደረግሁትም ሰዎቹ በእስራኤል ዘንድ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ስለ ፈጸሙ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ የቁባቴን አስከሬን ወስጄ ቈራረጥሁት፤ እነርሱ ይህን የመሰለ ክፉ በደል ስለ ሠሩ የቈራረጥኋቸውን ቊርጥራጮች ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላክሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እኔም ዕቅ​ብ​ቴን ይዤ በመ​ለ​ያ​ያዋ ቈራ​ረ​ጥ​ኋት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እን​ደ​ዚህ ያለ ስን​ፍና ስለ ሠሩ ወደ እስ​ራ​ኤል ርስት አው​ራጃ ሁሉ ሰደ​ድሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እኔም ቁባቴን ይዤ ቈራረጥኋት፥ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ኃጢአትና ስንፍና ስለ ተሠራ ወደ እስራኤል ርስት አገር ሁሉ ሰደድሁ።

See the chapter Copy




መሳፍንት 20:6
9 Cross References  

ቤቱ እንደደረሰም ቢላዋ አንሥቶ ቁባቱን ዐሥራ ሁለት ቦታ በመቈራረጥ ወደ እስራኤል ምድር ሁሉ ሰደደ።


የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።


እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የጌታን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል ፈጽሟልና እርሱና የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠል።’ ”


የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።


ከመላው የእስራኤል ነገዶችም ለሠራዊቱ ስንቅ እንዲይዙ፥ ከመቶው ዐሥር፥ ከሺው አንድ መቶ፥ ከዐሥር ሺው ደግሞ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን። ከዚያም ሠራዊቱ በብንያም ወደምትገኘው ጊብዓ በሚደርስበት ጊዜ፥ ነዋሪዎችዋ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት አስነዋሪ ድርጊት ተገቢውን ቅጣት ይሰጣቸዋል።”


“በእነዚህ ሁሉ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ ረክሰዋልና በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ።


ስለዚህ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ የተደረገውን ጸያፍ ወግ ሁሉ ፈጽሞ እንዳታደርጉ፥ በእርሱም ራሳችሁን ፈጽሞ እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”


በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፥ ጥቂት የከተማይቱ ወስላቶች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፥ “ዝሙት እንድንፈጽም በት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements